• ወደ ዓለም አቀፉ ድረ-ገጽ ይመለሱ
WageIndicator Logo
ኢትዮጵያ ውስጥ ስራChevron
የምንሰራውChevron
ስለ እኛChevron
Search
ያግኙን
arrow
ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ
የበለጠ ለማወቅ ይህንን ክፍል ያስሱ።
ዝቅተኛ ክፍያ
የመኖሪያ ደመወዝ
ደመወዝArrow
የአሠሪና ሠራተኛ ሕግArrow
የደምወዝ የዳሰሳ ጥናት
ስራና ደመወዝን
ደመወዝና የሥራ ሰዓት
የዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራት
ውሎችና ስንብቶች
የቤተሰብ ሀላፊነቶች
ወሊድ እና ሥራ
ጤንነትና ደህንነት በስራ ቦታ
ስራና ህመም
ማህበራዊ ዋስትና
በስራ ቦታ ፍትሀዊ አያያዝ
የሰራተኛማህበራት መብት
ሁሉንም ርዕሶች ያስሱ
የምንሰራው
የበለጠ ለማወቅ ይህንን ክፍል ያስሱ።
መረጃ እና አገልግሎቶች
ፕሮጀክቶች [ENG]
ክስተቶች [ENG]
ህትመቶች [ENG]
ዜና እና ታሪኮች [ENG]
ስለ እኛ
የበለጠ ለማወቅ ይህንን ክፍል ያስሱ።
ማን እንደሆንንArrow
አጋሮቻችን [ENG]
የምንሰራባቸው ቦታዎች [ENG]
ፖሊሲዎቻችን እና እቅዶቻችን [ENG]
የፕሬስ ክፍል [ENG]
ያግኙን [ENG]
ከእኛ ጋር ይስሩ [ENG]
ስልጠና ስራዎች [ENG]
ታሪካችን
የዳታ ተጠቃሚዎች
Scroll left
Scroll right
  1. ኢትዮጵያ
  2. ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ
  3. የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ
  4. የዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራት

የዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራት

ይህ ገጽ ለመጨረሻ ጊዜ ተዘምነ: 2026-01-07

ከክፍያ ጋር ዕረፍት/ አመታዊ ፈቃድ

ለመጀመሪያ አንድ ዓመት የአገልግሎት ጊዜ: ሠራተኞች 16 የሥራ ቀናት፤ እንዲሁም ከአንድ ዓመት በላይ ለተበረከተ አገልግሎት: ለእያንዳንዱ ሁለት የአገልግሎት ዓመታት: አንድ የሥራ ቀን እየተጨመረ የዓመት ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጣል፡፡5 አመት አገልግሎት ያለው ሰራተኛ 18 የሥራ ቀናት ከክፍያ ጋር የዓመት ፈቃድ ያገኛል (1 ተጨማሪ ቀን በየሁለት ዓመት)፡፡

አንድ ሠራተኛ የመጀመሪያውን የዓመት እረፍት ከአንድ ዓመት አገልግሎት በኋላ የመውሰድ መብት ሲኖረው፤ ቀጣዩንና ተከታዮቹን የዓመት እረፍት ቀጣሪው በሚያዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ሰራተኛው ከፈለገ/ገች እና መደበኛ ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ አስፈላጊ ሲሆን በእያንዳንዱ የካሌንደር ዓመት ውስጥ ሊወስድ ይችላል፡፡ አንድ ሠራተኛ በአሰሪው ፍቃድ እረፍቱን በሁለት በመክፈል ለመውስድ ወይም እስከ ሁለት ዓመት ድረስ እንዲያስተላልፍለት አሰሪውን ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ለውጥ ሁለት ተከታታይ አመታት ሊበልጥ አይችልም፡፡

አንድ ሰራተኛ የአመት ፍቃድ መብቱን ሳይጠቀም የስራ ውሉ ቢቋረጥ በአገልግሎት ዘመኗ/ኑ ርዝማኔ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የእረፍት ማካካሻ ይደረግለታል/ላታል፡፡ ከዚህ ድንጋጌ በተጨማሪ ለአመት እረፍት ማካካሻ የሚሰጥ ወይም የሚከፈልበት የአመት እረፍት መብትን የሚሽር ወይም የሚሰርዝ ወይም የሚያስቀር ማንኛውም ስምምነት፣ የህብረት ስምምነት ወይም ሌላ ስምምነት ውድቅ እና ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ አንድ ሰራተኛ በአመት እረፍቱ ጊዜ ቢታመም ከህመም ፍቃድ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የአመት እረፍት ሊቋረጥ የሚችል ሲሆን አሰሪው በአመት እረፍት ላይ ያለን ሰራተኛ መጥራት የሚችለው ያልታሰቡ ሁኔታዎች ተከስተው የሰራተኛውን በስራው ላይ መገኘት ሲያስፈልግ ብቻ ይሆናል፡፡ ከእረፍት ላይ የተጠራ ሰራተኛ በጉዞ ላይ ያጠፋውን ሰዓት ሳይጨምር የቀሪ እረፍት ጊዜውን የሚሸፍን ክፍያ የማግኘት መብት ያለው ሲሆን አሰሪው ሰራተኛው በመጠራቱ ምክንያት በቀጥታ ለሚያጋጥመው ወጪ ሁሉ እና ውሎ አበል ወጪዎችን መሸፈን ይኖርበታል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 76-80

በህዝባዊ በዓላት ወቅት ክፍያ

በህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት ወቅት: ሰራተኞች ከሙሉ ክፍያ ጋር ዕረፍት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህም መታሰቢያ እና ሀይማኖታዊ /ክርስቲያንና ሙስሊም/ በዓላትን ይጨምራል፡፡ ህዝባዊ በዓላት አብዛኛውን ጊዜ በቁጥር 13 ናቸው፡፡ እነዚህም ቀናት ገና (ታህሳስ 29)፣ የነቢዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ)፣ ጥምቀት (ጥር 11)፣ የአድዋ ድል (የካቲት 23)፣ ስቅለት (ሚያዝያ 10)፣ ትንሣዔ (ሚያዝያ 12)፣ ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን (ሚያዝያ 23)፣ የኢትዮጵያ አርበኞች መታሰቢያ (ሚያዝያ 27)፣ የደርግ መንግስት የወደቀበት (ግንቦት 20)፣ ኢድ አልፈጥር ረመዳን፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት (መስከረም 1)፣ መስቀል (መስከረም 17) እና ኢድ አል አድሐ/አረፋ ናቸው፡፡ (የሙስሊም በዓላት በጨረቃ ካላንደር መሠረት ናቸው)፡፡

አንድ የሕዝብ በዓል ከሌላ የሕዝብ በዓል ጋር ቢደረብ ወይም በሕግ በተወሰነ የዕረፍት ቀን ላይ ቢውል በዚህ ቀን የሠራ ሠራተኛ ክፍያ የሚደረግለት በአንዱ የሕዝብ በዓል ብቻ ይሆናል፡፡

ሰራተኛው በአንድ ቀን ለተከበሩ ክብረ በአላት፡ ድርብ ካሳ መቀበል አይችልም። ቀጣሪዎችም እንዲሁ በዓላትን ለማካካስ ተጨማሪ የዕረፍት ቀን መስጠት አይጠበቅባቸውም።

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 73-75፣ በ1975 የወጣው እና በ1996 የተሻሻለው የህዝባዊ ክብረ በዓላት እና እረፍት ቀናት አዋጅ፡፡

ሳምንታዊ የዕረፍት ቀን

ሰራተኞች በሳምንት ለ24 ተከታታይ ሰዓታት እረፍት የማግኘት መብት አላቸው፡፡ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በመርህ ደረጃ ለሁሉም ሰራተኞች እሁድ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ በስራው ባህሪ ምክንያት ሳምንታዊ የእረፍት ቀን እሁድ ላይ መስጠት የማይቻል ከሆነ ሌላ ቀን እንደ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በምትክ ይሰጣል፡፡ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን ከጠዋቱ 12፡00ሰዓት እስከ ቀጣዩ ቀን 12፡00ሰዓት ጠዋት ያለውን ጊዜ ይጨምራል፡፡ የስራው ባህሪ ወይም በአሰሪው የሚሰራው አገልግሎት ባህሪ በእሁድ ቀን የሳምንት እረፍት የማያሰጥ ከሆነ ሌላ ቀን እንደ ሳምንታዊ የእረፍት ቀን በምትክነት ሊሰጥ ይችላል፡፡

ምንጭ፡ የአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2019 አንቀጽ 69

ስራና በዓላትን የተመለከቱ ደንቦች

  • የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 1156/2011 / Labour Proclamation No. 1156/2019
  • በ1975 የወጣው እና በ1996 የተሻሻለው የህዝባዊ ክብረ በዓላት እና እረፍት ቀናት አዋጅ / Public Holidays and Rest Day Proclamation 1975, amended in 1996

ተያያዥ ርዕሶች

ደመወዝና የሥራ ሰዓት ስራና ደመወዝን ወሊድ እና ሥራ ስራና ህመም
ተዛማጅ ገጾች
ስራና ደመወዝንደመወዝና የሥራ ሰዓትየዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራትውሎችና ስንብቶችማሳሰቢያ እና የስራ ስንብት ክፍያየቤተሰብ ሀላፊነቶችወሊድ እና ሥራከስራ ከመባረር ጥበቃለሰራተኛ ሴቶች የማጥባት ዕረፍትጤንነትና ደህንነት በስራ ቦታስራና ህመምየአካል ጉዳት /የስራ ላይ ጉዳት ጥቅምማህበራዊ ዋስትናየስራ አጥነት ጥቅምበስራ ቦታ ፍትሀዊ አያያዝየስራ ቦታ ወሲባዊ ትንኮሳህፃናት በስራ ቦታየግዳጅ ስራየሰራተኛማህበራት መብት

ይህን ገጽ ጥቀስ: © WageIndicator 2026  –  ኢትዮጵያ  –  የዓመት ዕረፍት እና በሳምንታዊና በህዝብ በዓላት መስራት, ከክፍያ ጋር ዕረፍት, አመታዊ ፈቃድ - ኢትዮጵያ
FacebookLinkedin
ስለ WageIndicator የበለጠ ይወቁ
ከ WageIndicator ቡድን ጋር ይገናኙ እና ስለ ሥራችን የበለጠ ይወቁ
ተጨማሪ ያንብቡ Go to the about us page
arrow
ያግኙን Go to the contact form
arrow
WageIndicator Logo
WageIndicator ኢትዮጵያ
ለተግባር የሚውል መረጃ
WageIndicator Foundation በዓለም አቀፍ ደረጃ በዝቅተኛ ደመወዝ፣ የመኖሪያ ደመወዝ፣ የመኖሪያ ታሪፍ እና የመኖሪያ ገቢ፣ ሥራዎች እና ደመወዞች፣ የአሰሪና ሠራተኛ ሕግ፣ የኅብረት ስምምነቶች፣ እንዲሁም በጊግ ሥራ እና የፕላትፎርም ኢኮኖሚ ዙሪያ መረጃዎችን የሚሰበስብ፣ የሚያወዳድር እና የሚያጋራ ገለልተኛ እና ለትርፍ ያልቆመ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። እ.ኤ.አ. በ2000 የጀመርን ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በ208 አገሮች እና ግዛቶች ውስጥ እንንቀሳቀሳለን።
ስራ እና መረጃ
ዝቅተኛ ደመወዝ
የመኖሪያ ደመወዝ
የደመወዝ ማጣሪያ
የአሰሪና ሠራተኛ ሕግ
የኅብረት ስምምነቶች
መረጃ እና አገልግሎቶች
የቅርብ ጊዜ መረጃዎች
ፕሮጀክቶች
ክስተቶች
ዜናዎች
ህትመቶች
ስለ እኛ
ማን እንደሆንን
ከእኛ ጋር ይሥሩ
ፖሊሲዎቻችን እና እቅዶቻችን
የፕሬስ ክፍል
FacebookInstagramLinkedinYoutube
Privacy PolicyCookies StatementWebsite Terms & ConditionsAccessibilityPowered by the WageIndicator Foundation