ስለ እኛ
የ WageIndicator ፋውንዴሽን ዓለም አቀፍ፣ ገለልተኛ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። በአሁኑ ጊዜ ከ208 በላይ በሚሆኑ አገራት እና ግዛቶች እንንቀሳቀሳለን። ተልዕኳችን በዓለም ዙሪያ የሥራ ገበያ ግልፅነትን ማሳደግ ሲሆን፤ ለሠራተኞች፣ ለአሠሪዎች፣ ለተመራማሪዎች እና ለፖሊሲ አውጪዎች ፍትሐዊ ውሳኔ አሰጣጥን የሚያግዙ መረጃዎችን በማቅረብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሥራ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ ማስቻል ነው።
እኛ ማን ነን
እኛ ቆራጥ፣ ግልፅ፣ በዓላማ የምንመራ፣ ትክክለኛ እና ተልዕኮ ያነገብን ነን። እኛ የ WageIndicator ፋውንዴሽን ነን፤ ዓለም አቀፍ እና ገለልተኛ የሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነን። ዓላማችን እርስዎ የተሻለ ውሳኔ ማሳለፍ እንዲችሉ መረጃን ማጋራት ነው። እ.ኤ.አ ከ1999 ጀምሮ፣ ስለ ዝቅተኛ ደመወዝ፣ የመኖሪያ ደመወዝ፣ ሥራዎች እና ደመወዞች፣ የአሰሪና ሠራተኛ ሕግ፣ የኅብረት ስምምነቶች እና የሥራ ሁኔታዎች ግልጽ መረጃን ስንሰበስብ እና ስናቀርብ ቆይተናል። ትክክለኛ እና የተሟላ፣ ለመረዳት ቀላል እና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ መረጃ በማጋራታችን ኩራት ይሰማናል። ማንም ይሁኑ የትም ይኑሩ፣ ለእርስዎ ዐውድ አግባብነት ያለው መረጃ በራስዎ ቋንቋ ልንሰጥዎ ዓላማችንን እናደርጋለን።
ስለ እኛ የበለጠ ይወቁ
የመረጃ ቋቶቻችን
መረጃ እና አገልግሎቶች
ለድርጅትዎ ሠራተኞች ወይም በአቅርቦት ሰንሰለትዎ ውስጥ ላሉ ሠራተኞች የመኖሪያ ደመወዝ እና/ወይም የመኖሪያ ገቢ ግምቶችን እየፈለጉ ነው? የ WageIndicator ፋውንዴሽን በዓለም ዙሪያ ካሉት ትልልቅ የመኖሪያ ደመወዝ የመረጃ ቋቶች አንዱን ያቀርባል።





