የምንሰራው
ምን እንደምንሠራ ይመልከቱ
በመረጃዎቻችን እና በፕሮጀክቶቻችን አማካኝነት ለሠራተኞች፣ ለአሰሪዎች፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለሠራተኛ ማኅበራት እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ምሁራን የሥራ ገበያ ግልጽነትን ለማሳደግ ዓላማ አለን። ስለ ሥራዎች እና ደመወዞች፣ ዝቅተኛ ደመወዝ፣ የመኖሪያ ደመወዝ፣ የመኖሪያ ገቢ እና የመኖሪያ ታሪፍ፣ የአሰሪና ሠራተኛ ሕግ፣ የኅብረት ስምምነቶች፣ የጊግ ሥራ እና የፕላትፎርም ኢኮኖሚ እንዲሁም የሥራ የወደፊት ሁኔታን (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ጨምሮ) መረጃዎችን እንሰበስባለን፣ እንተነትናለን፣ እናጋራለን። እነዚህ መረጃዎች እና የመረጃ ቋቶች ለአካዳሚክ ምርምር፣ ለማኅበራዊ ውይይቶች እና ለ(ደመወዝ) ድርድር፣ በፖሊሲ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር፣ ለጥቅምና መብት ጥበቃ ዘመቻዎች (advocacy)፣ ለሪፖርት መስፈርቶች እና ለዘላቂ የልማት ግቦች (SDGs) ትግበራ አገልግሎት ላይ ይውላሉ።

የሥራ ዓለም
በዓለም ዙሪያ ከ200 በላይ በሚሆኑ አገሮች እና ግዛቶች ውስጥ ገለልተኛ እና ተደራሽ የሥራ ገበያ መረጃዎችን እናቀርባለን። መረጃዎቻችን ከ70 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በየጊዜው የሚዘመኑ ሲሆን፣ በየዓመቱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ይደርሳሉ። የመረጃ ቋቶቻችን የቅርብ ጊዜዎቹን ሕጋዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክንውኖች ለማንፀባረቅ በየወሩ፣
ምን እንደምንሰራ
ስለ ሥራ ገበያ፣ ስለ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ስለ የመኖሪያ ደመወዝ ዓለም አቀፍ ግንዛቤዎችን እንሰጣለን፤ እንዲሁም በዓለም ዙሪያ መረጃ እንዲደርሶት ፕሮጀክቶችን፣ ምርምሮችን፣ ኩነቶችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ፖድካስቶችን፣ ዜናዎችን እና ምስላዊ መረጃዎችን እናጋራለን።